ስጦታ ደግሞም የመንፈስ ስጦታዎች; የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተመልከቱ እግዚአብሔር ብዙ በረከቶችና ስጦታዎች ለሰው ይሰጣል። ብዙ መንፈሳዊ ስጦታዎች አሉ, ፩ ቆሮ. ፲፪፥፬–፲. የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ, ፩ ቆሮ. ፲፪፥፴፩. በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ናቸው, ያዕ. ፩፥፲፯. የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የእግዚአብሔር ስጦታ ነው, ፩ ኔፊ ፲፥፲፯. ስጦታዎች የሉም የሚሉት የክርስቶስ ወንጌልን አያውቁም, ሞር. ፱፥፯–፰. ሁሉም ጥሩ ስጦታዎች ከክርስቶስ ይመጣሉ, ሞሮኒ ፲፥፰–፲፰. ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነውን ዘላለማዊ ህይወት ነው, ት. እና ቃ. ፲፬፥፯ (፩ ኔፊ ፲፭፥፴፮). ስጦታዎች እግዚአብሔርን ለሚያፈቅሩት ይሰጣል, ት. እና ቃ. ፵፮፥፰–፲፩. ሁሉም እያንዳንዱ ስጦታ አልተሰጣቸውም, ት. እና ቃ. ፵፮፥፲፩–፳፱.