ነፍስ
ቅዱሳት መጻህፍት ስለነፍስ በሶስት መንገዶች ያናገሩባቸዋል፥ (፩) ከምድረ ህይወት በፊት እና ከምድረ ህይወት በኋላ ያሉ መንፈሶች (አልማ ፵፥፲፩–፲፬፤ አብር. ፫፥፳፫)፤ (፪) በአለሟችነት አንድ የሆነ መንፈስ እና ሰውነት (ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፭፤ አብር. ፭፥፯)፤ እናም (፫) መንፈሱና ሰውነቱ እንደገና ለመለየት በማይቻል ሁኔታ አንድ የሆኑለት የማይሞት፣ ከሞት የተነሳ ሰው (፪ ኔፊ ፱፥፲፫፤ ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፭–፲፮)።
የነፍሶች ዋጋ
ሁሉም ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው። ስለእያንዳንዱ ልጆቹ ሀሳብ አለው እናም እያንዳንዱንም እንደ አስፈላጊ ይመለከታቸዋል። ልጆቹ ስለሆኑም፣ እንደ እርሱ የመሆን ችሎታ አላቸው። ስለዚህ፣ ታላቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው።