ኩራት ደግሞም ሀብቶች; ትሁት፣ ትሕትና; አለማዊነት; ከንቱ፣ ከንቱነት; ገንዘብ ተመልከቱ ትሕትና ወይም የመማር ችሎታ የሌለው። ትዕቢት ሰዎችን እርስ በራስ እና ከእግዚአብሔር ጋር የተቃረኑ እንዲሆኑ ያደርጋል። ትዕቢተኛ ሰው በአካባቢው ከሚገኙት እራሱን ከፍ ያደርጋል እናም የእግዚአብሔርን ፍላጎት ሳይሆን የእራሱን ፍላጎት ይከተላል። ጉረኛነት፣ ቅናት፣ ልበ ደንዳናነት፣ እና ኩራተኝነት የትዕቢተኛ ሰው ጸባይ ናቸው። እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፣ ልብህ እንዳይጓደድ, ዘዳግ. ፰፥፲፩–፲፬. ትዕቢትንና እብሪትን እጠላለሁ, ምሳ. ፰፥፲፫ (ምሳ. ፮፥፲፮–፲፯). ትዕቢት ጥፋትን ይቀድማል, ምሳ. ፲፮፥፲፰. የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛው ላይ ይሆናል, ኢሳ. ፪፥፲፩–፲፪ (፪ ኔፊ ፲፪፥፲፩–፲፪). የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል, አብድ. ፩፥፫. ትዕቢተኞች ሁሉ ገለባ ይሆናሉ, ሚል. ፬፥፩ (፩ ኔፊ ፳፪፥፲፭; ፫ ኔፊ ፳፭፥፩; ት. እና ቃ. ፳፱፥፱). ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል, ማቴ. ፳፫፥፲፪ (ት. እና ቃ. ፻፩፥፵፪). እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል, ፩ ጴጥ. ፭፥፭. ትልቁና ሰፊው ህንፃ የዓለም ኩራት ነው, ፩ ኔፊ ፲፩፥፴፮ (፩ ኔፊ ፲፪፥፲፰). በተማሩ ጊዜ ራሳቸውን እንደብልህ ይቆጥራሉ, ፪ ኔፊ ፱፥፳፰–፳፱. በልባችሁ ኩራት ከፍ ብላችኋል, ያዕቆ. ፪፥፲፫፣ ፲፮ (አልማ ፬፥፰–፲፪). ከኩራታችሁስ ተገፍፋችኋልን, አልማ ፭፥፳፰. በህዝቡ ልብ ውስጥ ታላቅ ኩራት ገባ, ሔለ. ፫፥፴፫–፴፮. በኩራት ለመወጠር ምንኛ ፈጣን ናቸው, ሔለ. ፲፪፥፬–፭. የዚህ ሀገር ኩራት እንደሚጠፉ አረጋግጦአል, ሞሮኒ ፰፥፳፯. ኩራትን ተጠንቀቁ፣ አሊያም እንደ ኔፋውያን ትሆናላችሁ, ት. እና ቃ. ፴፰፥፴፱. ኩራታችሁን እና ተራ አስተሳሰባችሁን ሁሉ አቁሙ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፳፩.