ነጻ ምርጫ ደግሞም መልስ መስጠት፣ ሂሳብ፣ ተጠያቂነት፣ ሀላፊነት; ነጻ፣ ነጻነት ተመልከቱ እግዚአብሔር ለመምረት እና በራሳቸው ለመስራት ለሰዎች የሰጣቸው ችሎታ እና እድል። ከዛፍ ሁሉ ለመብላት ነጻ ነህ, ዘፍጥ. ፪፥፲፮. የምታገለግለውን ዛሬ ምረጡ, ኢያ. ፳፬፥፲፭ (አልማ ፴፥፰; ሙሴ ፮፥፴፫). ሰው ካልተፈተነ በስተቀር ለራሱ ማድረግ አይቻለውም, ፪ ኔፊ ፪፥፲፭–፲፮. ሰዎች ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ ናቸው, ፪ ኔፊ ፪፥፳፯. እናንተ ነፃ ናችሁ፤ ለራሳችሁ እንድትሰሩ ተፈቅዶላችኋል, ሔለ. ፲፬፥፴. አንድ ሶስተኛውን የሰማይ ሰራዊቶች በነጻ ምርጫቸው ምክንያት እንዲተዉ አደረገ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፴፮. ዲያብሎስ የሰዎችን ልጆች ይፈትን ዘንድ ግድ ነው፣ ካልሆነ በራሳቸው ለራሳችወ መምረጥ አይችሉም, ት. እና ቃ. ፳፱፥፴፱. እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ይምረጥ, ት. እና ቃ. ፴፯፥፬. ሁሉም ሰው በሰጠሁት ስነምግባር መሰረት ይስራ, ት. እና ቃ. ፻፩፥፸፰. ሰይጣን የሰው ነጻ ምርጫ ለማጥፋት ፈለገ, ሙሴ ፬፥፫. ጌታ ለሰው ነጻ ምርጫውን ሰጠው, ሙሴ ፯፥፴፪.