እርካታ
በተራራ ስብከት ውስጥ የተነጠረ እና መንፈሳዊ ጸባይን በመግለፅ ኢየሱስ የሰጣቸው የተከታተሉ ትምህርቶች (ማቴ. ፭፥፫–፲፪፤ ሉቃ. ፮፥፳–፳፫)። ክርስቶስ ስለተባረኩት የተናገራቸው አረፍተ ነገሮች የተዘጋጁት እያንዳንዱ አባባል ከዚያ በኋላ በሚመጣው ላይ እየገነባ በሚሄድበት መንገድ ነው። ክርስቶስ ስለተባረኩት የተናገራቸው አረፍተ ነገሮች በፍጹም እና በትክክለኛነት በ፫ ኔፊ ፲፪ ውስጥ ይገኛሉ።