እጅን መጫን ደግሞም ለታመሙት አገልግሎት መስጠት; መለየት; መሾም፣ ሹመት; የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተመልከቱ እንደ ክህነት ስነስርዓት ክፍል፣ እጆችን በሰው ራስ ላይ መጫን። እንደ ሹመቶች፣ በረከቶች፣ ለታመሙት አገልግሎት የመስጠት፣ የቤተክርስቲያን አባልነትን የማረጋገጥ፣ እና መንፈስ ቅዱስን የመስጠት እይነት ብዙ የክህነት ስነስርዓቶች የሚከናወኑት እጆችን በመጫን ነው። ሙሴ ጌታ እንዳዘዘው፣ እጁን በኢያሱ ራስ ላይ ጫነ, ዘኁል. ፳፯፥፲፰፣ ፳፪–፳፫ (ዘዳግ. ፴፬፥፱). ኢየሱስም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ፈወሰ, ማር. ፮፥፭ (ሞር. ፱፥፳፬). ሐዋሪያት ሰባቶቱ ረዳቶቻቸው ላይ እጃቸውን ጫኑ, የሐዋ. ፮፥፭–፮. መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው እጅን በመጫን ነበር, የሐዋ. ፰፥፲፬–፲፯. ሐናንያ በሳውል ላይ እጁን ጫነ እና አይኑ እንዲያይ አደረገ, የሐዋ. ፱፥፲፪፣ ፲፯–፲፰. ጳውሎስም እጁንም በላዩ ጭኖ ፈወሰው, የሐዋ. ፳፰፥፰. ጳውሎስ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን አስተማረ, ዕብ. ፮፥፪. አልማ እጁን በመጫን ካህናትን እና ሽማግሌዎችን ሾመ, አልማ ፮፥፩. ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ እጃቸውን በመጫን መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት ኃይል ሰጣቸው, ፫ ኔፊ ፲፰፥፴፮–፴፯. እጃችሁን በምትጭኑበት ላይ መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት ስልጣን ይኖራችኋል, ሞሮኒ ፪፥፪. ሽማግሌዎችም እጆቻቸውን ልጆቹ ላይ ይጫኑ, ት. እና ቃ. ፳፥፸. እጆችን በመጫን መንፈስ ቅዱስን ይቀበላሉ, ት. እና ቃ. ፴፭፥፮ (እ.አ. ፩፥፬). ሽማግሌዎች እጆቻቸውን በታመሙት ላይ ይጫኑ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፵፬ (ት. እና ቃ. ፷፮፥፱). ልጆችም ከጥምቀት በኋላ የእጆችን ጭነት ይቀበሉ, ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፯. ክህነት ለመቀበል የሚቻለው እጅን በመጫን ነው, ት. እና ቃ. ፹፬፥፮–፲፮.