መሾም፣ ሹመት ደግሞም ሀላፊነት፣ ሀላፊ; ስልጣን; እጅን መጫን; ክህነት; ጥሪ፣ በእግዚአብሔር መጠራት፣ የተጠራበት ተመልከቱ ስልጣን ወይም ሀላፊነትን መመደብ ወይም መስጠት። በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ በስልጣን ለመጠቀም፣ ሰው በእግዚአብሔር፣ በትንቢት፣ እና ስልጣን ባላቸው በእጆች በመጫን መጠራት አለበት (እ.አ. ፩፥፭)። ምንም እንኳን ሰው በመሾም ስልጣንን ለማግኘት ቢችልም፣ ለዚህ ስልጣን ልዩ ቁልፍ ባላቸው መመሪያ ነው የሚጠቀምበት። ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ, ኤር. ፩፥፭. እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፣ ሾምኋችሁ, ዮሐ. ፲፭፥፲፮. ከእግዚአብሔር ስልጣን ኖሮት ካህናትን ሾመ, ሞዛያ ፲፰፥፲፰. ሰዎች በከፍተኛው ክህነት በቅዱስ ስነስርዓቶች ተሾሙ, አልማ ፲፫፥፩–፱. ኢየሱስ አስራሁለቱን ሐዋርያት ጠራቸው እናም ስልጣንን ሰጣቸው, ፫ ኔፊ ፲፪፥፩. ሽማግሌዎች ካህናትን እና መምህሮችን እጆችን በመጫን ሾሙ, ሞሮኒ ፫. ስላልተሾማችሁ ለትንሽ ጊዜ መቆየት አለባችሁ, ት. እና ቃ. ፭፥፲፯. ጆሴፍ ስሚዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋሪያ እንዲሆን ተሾመ, ት. እና ቃ. ፳፥፪ (ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፪). ካለቤተክርስቲያኗ ምርጫ ማንም ሰው በቤተክርስቲያን ሀላፊነት አይሾምም, ት. እና ቃ. ፳፥፷፭. ስልጣን ባለው ካልተሾመ በስተቀር፣ ለማንም ወንጌሌን እንዲሰብክ አይሰጠውም, ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፩. ሽማግሌዎች ወንጌልን ለመስበክ ተሹመዋል, ት. እና ቃ. ፶፥፲፫–፲፰. የቤተክርስቲያኗን ሌሎች ሀላፊዎች መሾም እና ማስተካከልም የአስራ ሁለቱ ሀላፊነት ነው, ት. እና ቃ. ፻፯፥፶፰. የአባቶችን በረከቶች ለማግኘት እና ይህንንም ለማስተዳደር መብትም ለማግኘት ለመሾም ፈለኩኝ, አብር. ፩፥፪. ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ እርስ በራስ ወደ አሮናዊ ክህነት ተሾሙ, ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፷፰–፸፪.