ቲለስቲያል ክብር ደግሞም የክብር ደረጃዎች ተመልከቱ ከመጨረሻው ፍርድ በኋላ ሰዎች ከሚኖሩባቸው ከሶስቱ የክብር ደረጃዎች ዳግማዊ። ጳውሎስ የከዋክብትም ክብርን አየ, ፩ ቆሮ. ፲፭፥፵–፵፩. ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን የቲለስቲያል ክብርን ተመለከቱ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፹፩–፺. የቲለስቲያል አለም ኗሪዎች እንደ ከዋክብት ለመቆጠር የማይችሉ ናቸው, ት. እና ቃ. ፸፮፥፻፱–፻፲፪. በቲለስቲያል መንግስት ህግ መፅናት የማይችለውም በቲለስቲያል ክብር መፅናት አይችልም, ት. እና ቃ. ፹፰፥፳፬፣ ፴፩፣ ፴፰.