መነሳሻ፣ መነሳሳት ደግሞም መንፈስ ቅዱስ; ራዕይ ተመልከቱ ለሰው በእግዚአብሔር የተሰጠው መኮታዊ አመራር። መነሳሳት ከመንፈስ የሚመጣው በተለያዩ መንገዶች ወደ ሰው አዕምሮና ልብ ነው። ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ, ፩ ነገሥ. ፲፱፥፲፪. መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል, ዮሐ. ፲፬፥፳፮. የእውነት መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል, ዮሐ. ፲፮፥፲፫. ማድረግ ያለብኝን ነገሮች ቀድሜ ሳላውቅ በመንፈስ ተመራሁ, ፩ ኔፊ ፬፥፮. የጌታ ድምፅ በአዕምሮዬ መጣ, ኢኖስ ፩፥፲. ያለማቋረጥ መልካምን እንዲሰሩ የሚጋብዝ እናም የሚገፋፋ በእግዚአብሔር የሚነሳሳ ነው, ሞሮኒ ፯፥፲፫–፲፮. በአምሮህ ሰላምን አልተናገርኩህምን, ት. እና ቃ. ፮፥፳፫. በአዕምሮህ እና በልብህ እነግርሃለሁ, ት. እና ቃ. ፰፥፪. መንፈሴ አእምሮህን ያብራራል፣ ነፍስህን በደስታ ይሞላል, ት. እና ቃ. ፲፩፥፲፫. በዛኑ ግዜ የምትናገርውን እና የምትጽፈውን ይሰጥሃል, ት. እና ቃ. ፳፬፥፮ (ት. እና ቃ. ፹፬፥፹፭). ትንሽ የዝምታ ለስላሳ ድምፅም በሁሉም ነገሮች አሾከሸከ እና ሰንጥቆ ገባ, ት. እና ቃ. ፹፭፥፮.