ቀንበር ደግሞም ደቀ መዛሙርት ተመልከቱ በእንስሳት ወይም በሰዎች አንገት ላይ አብረው እንዲተሳሰሩ የሚያደርጋቸው እቃ። የክርስቶስ ቀንበር የደቀ መዛሙርት ምሳሌ ነው፣ ነገር ግን የባርነት ቀንበር የመጨቆን ምሳሌ ነው። ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነው, ማቴ. ፲፩፥፳፱–፴. ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ, ፪ ቆሮ. ፮፥፲፬. በባርነት ቀንበር አትያዙ, ገላ. ፭፥፩. ማናችሁንም በባርነት ቀንበር ስር እንድናመጣችሁ አንፈልግም, አልማ ፵፬፥፪. የቅዱሳን ስቃይ የብረት ቀንበር፣ ይህም ጠንካራ ማስረያ፣ የሲኦል ሰንሰለቶች ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፳፫፥፩–፫፣ ፯–፰.