ያንግ፣ ብሪገም በዚህ ዘመን የመጀመሪያ ሐዋርያ እናም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሁለተኛ ፕሬዘደንት። ቅዱሳንን ወደ ምዕራብ ከናቩ፣ ኢለኖይ ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ መራቸው እናም በምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ታላቅ ፈር ቀዳጅ ነበር። ብሪገም ያንግ በአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ላይ ፕሬዘደንት እንዲሆን ተጠራ, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፻፳፯. ብሪገም ያንግ ለአገልግሎቱ ተሞግሷል እና ከወደፊት ወደውጪ ጉዞም ፋታ አገኘ, ት. እና ቃ. ፻፳፮. ጌታ ብሪገም ያንግን ቅዱሳን ወደ ምዕራብ ሲጓዙ እንዴት እንደሚያደራጅ መመሪያ ሰጠው, ት. እና ቃ. ፻፴፮. ብሪገም ያንግ በመንፈስ አለም ውስጥ ምርጥ ከነበሩት አንዱ ነበር, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፶፫.