ፍጥረታዊ ሰው ደግሞም ስጋዊ; የአዳም እና የሔዋን ውድቀት; ዳግመኛ መወለድን፣ ከእግዚአብሔር መወለድ ተመልከቱ በመንፈስ ቅዱስ በመነሳሳት ሳይሆን በጥልቅ ስሜት፣ በፍላጎት፣ እና በስጋ ስሜት ተፅዕኖ እንዲኖርበት የሚመርጥ ሰው። እንደዚህ አይነት ሰው ስጋዊ ነገሮች ቢገቡትም መንፈሳዊ ነገሮችን አያስተውልም። በአዳም እና ሔዋን ውድቀት ምክንያት ሰዎች ሁሉ ስጋዊ፣ ወይም ሟች፣ ናቸው። እያንዳንዱ ሰው ፍጥረታዊ ሰው መሆንን ለማቆም በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እንደገና መወለድ አለባቸው። ፍጥረታዊ ሰው የመንፈስን ነገር አይቀበለውም, ፩ ቆሮ. ፪፥፲፬. ተፈጥሮአዊው ሰው ለእግዚአብሔር ጠላት ነው እናም መቀየር ይገባዋል, ሞዛያ ፫፥፲፱. በስጋዊ ተፈጥሮው የቆየ፣ ወድቆ ይቀራል, ሞዛያ ፲፮፥፭ (አልማ ፵፪፥፯–፳፬; ት. እና ቃ. ፳፥፳). እነዚህን ነገሮች የሚያውቅ ተፈጥሯዊው ሰው ማን ነው, አልማ ፳፮፥፲፱–፳፪. በተፈጥሮአዊው ወይም በስጋዊ ሁኔታ ያሉ ሰዎች ከእግዚአብሔር ውጭ ናቸው, አልማ ፵፩፥፲፩. በመተላለፉ ምክንያት፣ ሰው የመንፈስ ሞት ሞተ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፩. ማንም ተፈጥሮአዊ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመቋቋም አይችልም, ት. እና ቃ. ፷፯፥፲፪. ሰዎችም ስጋዊ፣ ስሜታዊና ዲያብሎሳዊ መሆን ጀመሩ, ሙሴ ፭፥፲፫ (ሙሴ ፮፥፵፱).