ያህዌህ
የእስራኤል አምላክ ቃል ኪዳን ወይም ትክክለኛ ስም። ይህም “ዘለአለማዊ ያለና የሚኖርን” ይጠቁማል (ዘፀአ. ፫፥፲፬፤ ዮሐ. ፰፥፶፰)። ያህዌህ የቅድመ ምድር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እናም ወደ ምድር እንደ ማርያም ልጅ መጣ (ሞዛያ ፫፥፰፤ ፲፭፥፩፤ ፫ ኔፊ ፲፭፥፩–፭)። ብዙም ጊዜ፣ ጌታ የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሲታይ፣ ይህም “ያህዌህ” ማለት ነው።
ያህዌህ ክርስቶስ ነው
ያህዌህ በጥንት ነቢያት የታወቀ ነው (ዘፀአ. ፮፥፫፤ አብር. ፩፥፲፮)። ሐዋሪያው ጳውሎስ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳን ያህዌህ እንደነበረ አስተማረ (ዘፀአ. ፲፯፥፮፤ ፩ ቆሮ. ፲፥፩–፬)። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የያሬድ ወንድም የቅድመ ምድር ክርስቶስን አየ እናም አመለከ (ኤተር ፫፥፲፫–፲፭)። ሞሮኒ ደግሞም ክርስቶስን “ያህዌህ” ብሎ ጠራ (ሞሮኒ ፲፥፴፬)። በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ ከሞት የተነሳውን ያህዌህ አዩ (ት. እና ቃ. ፻፲፥፫–፬)።