የሰው አለሟችነትን እና ዘለአለማዊ ህይወትን ለማምጣት የተነደፈ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት። ይህም እግዚአብሔር ከሰጣቸው ህግጋት፣ ስርዓቶች፣ እና ትምህርቶች ጋር ፍጥረትን፣ ውድቀትን፣ እና የኃጢያት ክፍያን በተጨማሪ የያዘ ነው። ይህ እቅድ ሁሉም ሰዎች ከፍ ከፍ እንዲሉና ከእግዚአብሔር ጋር ለዘለአለም ለመኖር እንዲችሉ ያደርጋል (፪ ኔፊ ፪፤ ፱)። በቅዱሳት መጻህፍት ደግሞም ይህ አላማ እንደ ደህንነት አላማ፣ የደስታ አላማ፣ እና የምህረት አላማ ተብሎ ይጠራል።