ፍርሀት ደግሞም መበርታት፣ ብርቱነት; ማክበር; እምነት፣ ማመን ተመልከቱ ፍርሀት ሁለት ትርጉሞች ሊኖሩት ይችላሉ፥ (፩) እግዚአብሔርን መፍራት ለእርሱ አምልኮትና አክብሮት መሰማት እናም ትእዛዛቱን ማክበር ነው፤ (፪) ሰውን፣ መጥፎ አደጋዎችን፣ ህመምንና፣ ክፉን መፍራትም ነው። እግዚአብሔርን መፍራት በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት የለም, ዘፍጥ. ፳፥፲፩. አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ, ዘዳግ. ፮፥፲፫ (ኢያ. ፳፬፥፲፬; ፩ ሳሙ. ፲፪፥፳፬). ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ, መዝ. ፪፥፲፩. የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው, መዝ. ፻፲፩፥፲. እግዚአብሔርን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ, ምሳ. ፫፥፯. እግዚአብሔርን ለሚፈሩት ደኅንነት እንዲሆን አውቃለሁ, መክ. ፰፥፲፪. በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ, ፊልጵ. ፪፥፲፪. እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት, ራዕ. ፲፬፥፯ (ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፬). ነቢያት በጌታ ፍርሃት ያለማቋረጥም ይጠበቁ ዘንድ ሁልጊዜም ያነሳሷቸዋል, ኢኖስ ፩፥፳፫. የጌታ ፍርሃት በአልማና በሞዛያ ልጆች ስለመጣባቸው በመሬት ላይ ወደቁ, አልማ ፴፮፥፯. በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በፊቱ የራሳችሁን መዳን ፈፅሙ, ሞር. ፱፥፳፯. የማይፈሩኝ፣ አውካቸዋለሁ፣ እንዲቀጠቀጡም አደርጋለሁ, ት. እና ቃ. ፲፥፶፮. እኔን የሚፈራም ስለሰው ልጅ መምጫ ምልክቶች ይጠብቃል, ት. እና ቃ. ፵፭፥፴፱. ሰውን መፍራት አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና, ዘፍጥ. ፳፮፥፳፬ (ኢሳ. ፵፩፥፲). እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፥ አትፍሩአቸው, ዘኁል. ፲፬፥፱. ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉና አትፍራ, ፪ ነገሥ. ፮፥፲፮. አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል, መዝ. ፶፮፥፬. የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ, ኢሳ. ፶፩፥፯ (፪ ኔፊ ፰፥፯). እግዚአብሔር የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም, ፪ ጢሞ. ፩፥፯. ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል, ፩ ዮሐ. ፬፥፲፰ (ሞሮኒ ፰፥፲፮). የሔለማን ልጆች ሞትን አልፈሩም, አልማ ፶፮፥፵፮–፵፰. የክፉዎችን ሁሉ ደረት የሞት ፍርሀት ሞላ, ሞር. ፮፥፯. ሰው ለማድረግ የሚችለውን አትፍሩ, ሞሮኒ ፰፥፲፮. ሰውን ከእግዚአብሔር አስበልጠህ መፍራት አልነበረብህም, ት. እና ቃ. ፫፥፯ (ት. እና ቃ. ፴፥፩፣ ፲፩; ፻፳፪፥፱). መልካምን ለማድረግ አትፍሩ, ት. እና ቃ. ፮፥፴፫. የቤተክርስቲያኔ ሰው የሆነ ሁሉ መፍራት የለበትም, ት. እና ቃ. ፲፥፶፭. ከተዘጋጃችሁ ፍርሀት አይኖራችሁም, ት. እና ቃ. ፴፰፥፴. ከፍርሀት ራሳችሁን አስወግዱ, ት. እና ቃ. ፷፯፥፲. ተደሰቱ፣ እናም አትፍሩ፣ እኔ ጌታ ከእናንተ ጋር ነኝና, ት. እና ቃ. ፷፰፥፮. ጠላቶቻችሁን አትፍሩ, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፲፯.