ካህን፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ደግሞም ሊቀ ካህን; የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተመልከቱ በእግዚአብሔር በፊት የሀይማኖት ስርዓትን ለሌሎች የሚያከናውን ሰው። በብዙ ጊዜ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ካህናት እንደ መልከ ጼዴቅ ስርዓት ሊቀ ካህናት ናቸው (አልማ ፲፫፥፪)። ከትንሳኤ በኋላ የእግዚአብሔርን ክብር ሙሉነት የሚቀበሉት በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ካህናትና ንጉሶች ይሆናሉ። መልከ ጼዴቅም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ, ዘፍጥ. ፲፬፥፲፰. እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ, መዝ. ፻፲፥፬ (ዕብ. ፭፥፮; ፯፥፲፯፣ ፳፩). ክርስቶስ ለአምላኩና ለአባቱ ካህናት እንድንሆን አደረገ, ራዕ. ፩፥፮ (ራዕ. ፭፥፲; ፳፥፮). ጌታ እግዚአብሔር ካህናት እንደ ቅዱስ ስርዓቱ እንደሾመ አስታውሱ, አልማ ፲፫፥፩–፳. በጻድቅ ትንሳኤ የሚመጡት ካህናት እና ንጉሶች ናቸው, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶፣ ፶፭–፷.