ሶስቱ ኔፋውያን ደቀ መዛሙርቶች ደግሞም ኔፋውያን; የተቀየሩ ሰዎች; ደቀ መዛሙርት ተመልከቱ በምመሐፈ ሞርሞን ውስጥ የተጠቀሱት ክርስቶስ ከመረጣቸው የኔፋውያን ደቀ መዛሙርት ሶስቱ። ጌታ ለእነዚህ ደቀ መዛሙርቶች ጌታ እንደገና እስከሚመጣ ድረስ ወደ ክርስቶስ ነፍሳትን በማምጣት በምድር ላይ እንዲቀሩ ለተወዳጁ ዮሐንስ የተሰጠውን አንድ አይነት በረከት ሰጣቸው። ምንም ስቃይ እንዳይሰማቸው እና እንዳይሞቱ ተቀይረው ነበር (፫ ኔፊ ፳፰)። እስከሚመጣ ድረስ እንዲቆዩ ዘንድ ክርስቶስ የሶስቱ ደቀ መዛሙርቶችን ፍላጎት ፈቀደ, ፫ ኔፊ ፳፰፥፩–፱. የሞት ስቃይ በጭራሽ አይደርስባቸውም, ፫ ኔፊ ፳፰፥፯–፱. ደስታቸው ሙሉ ይሆናል, ፫ ኔፊ ፳፰፥፲. ለጊዜ ወደ ሰማይ ተነጥቀው ነበር, ፫ ኔፊ ፳፰፥፲፫–፲፯. ህዝቡን አስተማሩ እናም ብዙ ስደትንም ተፅናኑ, ፫ ኔፊ ፳፰፥፲፰–፳፫. ሞርሞንን አስተማር, ፫ ኔፊ ፳፰፥፳፬–፳፮ (ሞር. ፰፥፲–፲፩). አህዛብን፣ አይሁዶችን፣ የተበተኑ ጎሳዎችን፣ እና ሁሉንም ሀገሮች ያስተምራሉ, ፫ ኔፊ ፳፰፥፳፯–፳፱. ሰይጣን በእነርሱ ላይ ስልጣን አይኖረውም, ፫ ኔፊ ፳፰፥፴፱.