ካሳ፣ ዳግም መመለስ ደግሞም የወንጌል ዳግም መመለስ ተመልከቱ ተወስዶ የነበረ ወይም የጠፋ ነገር ወይም ሁኔታ መመለስ። መንፈስና ሰውነት በፍጹም ሁኔታ ደግመው ይገናኛሉ, አልማ ፲፩፥፵፫–፵፬. ዳግም መመለስ ክፉን ለክፉ፣ ጻድቅን ለጻድቅ ማምጣት ነው, አልማ ፵፩፥፲–፲፭. በአስሩ ጎሳዎች ዳግም መመለስ እናም ምድርም ታድሳ እንደገነት አይነት ክብር እንደምትቀበልም እናምናለን, እ.አ. ፩፥፲ (ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፳፫–፳፬).