የቃል ኪዳን ምድር ጌታ ለታማኝ ተከታዮቹ፣ እናም በብዙ ጊዜ ለትውልዶቻቸው፣ እንደ ውርስ ቃል የሚገባላቸው ምድር። ብዙ የቃል ኪዳን ምድሮች አሉ። በብዙ ጊዜ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚናገሩበት የቃል ኪዳን ምድር በአሜሪካዎች ውስጥ ነው። ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ, ዘፍጥ. ፲፪፥፯ (አብር. ፪፥፲፱). የከነዓን ምድር ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ, ዘፍጥ. ፲፯፥፰ (ዘፍጥ. ፳፰፥፲፫). ሙሴ በከነዓን ውስጥ የእስራኤል ምድር ዳርቻን ወሰነ, ዘኁል. ፴፬፥፩–፲፪ (ዘኁል. ፳፯፥፲፪). ወደ ቃል ኪዳንም ምድር ትመራለህ, ፩ ኔፊ ፪፥፳ (፩ ኔፊ ፭፥፭). ጌታ ፃድቃንን በጣም አስፈላጊ ወደሆነው ምድር መራ, ፩ ኔፊ ፲፯፥፴፰. የሌሂ ትውልዶች የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ካከበሩ፣ በቃል ኪዳን ምድር ውስጥ ይበለፅጋሉ, ፪ ኔፊ ፩፥፭–፱. እስራኤል ወደ ቃል ኪዳን ምድር ትመለሳለች, ፪ ኔፊ ፳፬፥፩–፪ (ኢሳ. ፲፬፥፩–፪). ማንም ይህችን ምድር የራሱ ያደረገ ሀገር እግዚአብሔርን ያገለግላል፣ አለበለዚያ ይወገዳሉ, ኤተር ፪፥፱–፲፪. ፪ ስለዚህ፣ ይህም የቃል ኪዳን ምድር፣ እና ለፅዮን ከተማ ቦታም ነው, ት. እና ቃ. ፶፯፥፪. ይሁዳ ወደ አብርሐም ምድር ለመመለስ ይጀምሩ, ት. እና ቃ. ፻፱፥፷፬. አዲስቷ ኢየሩሳሌም በአሜሪካ ክፍለ አህጉር ትመሰረታለች, እ.አ. ፩፥፲.