መንገድ ደግሞም መራመድ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መራመድ (መሄድ); ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ ሰው የሚከተለው መንገድ ወይም አቅጣጫ። ኢየሱስ መንገዱ ነኝ አለ (ዮሐ. ፲፬፥፬–፮)። በመንገዱም እንድትሄድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ, ዘዳግ. ፰፥፮. ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው, ምሳ. ፳፪፥፮ (፪ ኔፊ ፬፥፭). መንገዴ ከመንገዳችሁ ከፍ ያለ ነው, ኢሳ. ፶፭፥፰–፱. ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና, ማቴ. ፯፥፲፫–፲፬ (፫ ኔፊ ፲፬፥፲፫–፲፬; ፳፯፥፴፫; ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፪፣ ፳፭). እግዚአብሔር ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል, ፩ ቆሮ. ፲፥፲፫. ጌታ ያዘዛቸውን ትዕዛዛት የሚሟሉበትን መንገድ ካላዘጋጀ በቀር ለሰው ልጆች ትዕዛዛትን አይሰጥም, ፩ ኔፊ ፫፥፯ (፩ ኔፊ ፱፥፮; ፲፯፥፫፣ ፲፫). በመግቢያው ካልሆነ በቀር ምንም ሌላ መንገድ የለም, ፪ ኔፊ ፱፥፵፩. በራሳችሁ ዘለዓለማዊውን ሞት ወይም የዘለዓለማዊውን ህይወት መንገድ እራሳችሁ ለመምረጥ ነጻነት አላችሁ, ፪ ኔፊ ፲፥፳፫. መንገዱ ይህ ነው፤ የተሰጠ ሌላ መንገድም ሆነ ስም የለምና, ፪ ኔፊ ፴፩፥፳፩ (ሞዛያ ፫፥፲፯; አልማ ፴፰፥፱; ሔለ. ፭፥፱). እግዚአብሔርም በልጁ ስጦታም ይበልጥ የተመረጠውን መንገድ አዘጋጅቷል, ኤተር ፲፪፥፲፩ (፩ ቆሮ. ፲፪፥፴፩). ሁልም ሰው በራሱ መንገድ ይጓዛል, ት. እና ቃ. ፩፥፲፮. ይህም በእኔ መንገድ መደረግ አለበት, ት. እና ቃ. ፻፬፥፲፮.