ክፉ፣ ክፋት ደግሞም ኃጢያተኛ፣ አመፃ; ኃጢያት; መንፈሳዊ ጭለማ; እድፍ፣ እድፍነት; እግዚአብሔርን የሚጠላ ተመልከቱ ክፋት፣ ኃጢያት፤ ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ታዛዥ አለመሆን። እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ, ዘፍጥ. ፴፱፥፯–፱. እግዚአብሔር ከኅጥኣን ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል, ምሳ. ፲፭፥፳፱. ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል, ምሳ. ፳፱፥፪ (ት. እና ቃ. ፺፰፥፱). በውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት, ፩ ቆሮ. ፭፥፲፫. መጋደላችን ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው, ኤፌ. ፮፥፲፪. ከክፉዎች ውጡ እናም ተለዩ፣ እናም የጎደፉ ነገሮቻቸውን አትንኩ, አልማ ፭፥፶፮–፶፯ (ት. እና ቃ. ፴፰፥፵፪). የኃጢአተኞች የመጨረሻ ሁኔታ ይህ ነው, አልማ ፴፬፥፴፭ (አልማ ፵፥፲፫–፲፬). ክፋት በፍፁም ደስታ ሆኖ አያውቅም, አልማ ፵፩፥፲. ኃጥአን የሚቀጡት በኃጢአተኞች ነው, ሞር. ፬፥፭ (ት. እና ቃ. ፷፫፥፴፫). በእዚያም ሰዓት ጻድቃኖችን ከኀጥያተኞቹ በሙሉ የሚለያዩበት ይመጣል, ት. እና ቃ. ፷፫፥፶፬. እንደዚህም የክፉዎች መጨረሻ ይመጣል, ጆ.ስ.—ማቴ. ፩፥፶፭.