ውግዘት ደግሞም አመጽ; ክህደት ተመልከቱ ማውገዝ ቤተክርስቲያኗ ከምትቀጣበት መንገድ በጣም ጥብቅ የሆነው ነው። የተወገዘ ሰው የቤተክርስትቲያን አባል አይደለም። የቤተክርስቲያን ባለስልጣኖች የጌታ ትእዛዛትን በመቃረን ለመኖር የሚመርጠውን እና በዚህም በቤተክርስቲያኗ አባል ለመሆን ብቁነትን የሚያጣውን ሰው ያወግዛሉ። የብዙዎች ልብ ጠጥሯል፣ ስማቸው ተደምስሷልና, አልማ ፩፥፳፬ (አልማ ፮፥፫). ንሰሃ ካልገባ፣ ከህዝቦቼ መካከል አይቆጠርም, ፫ ኔፊ ፲፰፥፴፩ (ሞዛያ ፳፮). የሚያመንዝር፣ እናም ንሰሃ የማይገባ፣ ወደ ውጭ ይጣላል, ት. እና ቃ. ፵፪፥፳፬. ኃጢያትን የሚሰራና ንስሃ የማይገባ ወደ ውጭ ይጣላል, ት. እና ቃ. ፵፪፥፳፰. አስፈላጊ የሆኑ ችግሮችን የማስተካከያ ስነስርዓቶች ተሰጥተዋል, ት. እና ቃ. ፻፪ (ት. እና ቃ. ፵፪፥፹–፺፫). ኤጲስ ቆጶስ የእስራኤል ዳኛ እንዲሆን ተመድቧል, ት. እና ቃ. ፻፯፥፸፪. ጻድቅ ህብረተሰቦች ሁሉ አባሎቻቸው በሚረብሹበት ጊዜ ለመቅጣት መብት, ት. እና ቃ. ፻፴፬፥፲.