መፅናት ደግሞም መፈተን፣ ፈተና; ትዕግስት; ጭንቀት ተመልከቱ ፈተና፣ ተቃዋሚነት፣ እና መከራ ቢኖርም ለእግዚአብሔር ትእዛዛት እውነት ለመሆን ፅኑ ውሳኔ ማድረግ። እስከ መጨረሻ የሚጸና ይድናል, ማቴ. ፲፥፳፪ (ማር. ፲፫፥፲፫). ለጊዜውም ነው እንጂ በእነርሱ ሥር የላቸውም, ማር. ፬፥፲፯. ፍቅር በሁሉ ይጸናል, ፩ ቆሮ. ፲፫፥፯. አብርሐም ከታገሰ በኋላ ተስፋውን አገኘ, ዕብ. ፮፥፲፭. እስከ መጨረሻ የሚፀኑ ከሆነ በመጨረሻው ቀን ከፍ ይደረጋሉ, ፩ ኔፊ ፲፫፥፴፯. ለትዕዛዛቱ ታዛዥ ከሆናችሁ እናም እስከመጨረሻው ከፀናችሁ ትድናላችሁ, ፩ ኔፊ ፳፪፥፴፩ (አልማ ፭፥፲፫). የክርስቶስን ቃል በመመገብ፣ እናም እስከመጨረሻው በመፅናት የምትቀጥሉ ከሆነ፣ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል, ፪ ኔፊ ፴፩፥፳ (፫ ኔፊ ፲፭፥፱; ት. እና ቃ. ፲፬፥፯). ስሜን በራሱ ላይ የወሰደ፣ እናም እስከመጨረሻው የፀና፣ እርሱ ይድናል, ፫ ኔፊ ፳፯፥፮. በቤተክርስቲያኔ እስከመጨራሻው የሚጸና በአለቴ ላይ የምመሰርተው እሱን ነው, ት. እና ቃ. ፲፥፷፱. በእምነት የሚጸና አለምን ያሸንፋታል, ት. እና ቃ. ፷፫፥፳፣ ፵፯. ዙፋናት እና አለቅነት ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በጉብዝና ለጸኑትም ሁሉ ይሰጧቸዋል, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፳፱.