የጥናት እርዳታዎች
ስነስርዓቶች


ስነስርዓቶች

ቅዱስ ስርዓቶች። ስነስርዓቶች መንፈሳዊ ትርጉም ያላቸው ስራዎችን የያዘ ነው። ደግሞም ስነስርዓቶች የእግዚአብሔር ህግጋት ማለት ናቸው።

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሚከናወኑ ስነስርዓቶች የታመሙትን ማስታመም (ያዕ. ፭፥፲፬–፲፭)፣ ቅዱስ ቁርባንን መባረክ (ት. እና ቃ. ፳፥፸፯፣ ፸፱)፣ በማጥለቅ መጠመቅ (ማቴ. ፫፥፲፮ት. እና ቃ. ፳፥፸፪–፸፬)፣ ልጆችን መባረክ (ት. እና ቃ. ፳፥፸)፣ መንፈስ ቅዱስን መስጠት (ት. እና ቃ. ፳፥፷፰፴፫፥፲፭)፣ ክህነትን መስጠት (ት. እና ቃ. ፹፬፥፮–፲፮፻፯፥፵፩–፶፪)፣ የቤተመቅደስ ስነስርዓቶችን (ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፴፱)፣ እና በአዲስና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን መጋባት (ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፲፱–፳) ናቸው።

የወኪል ስነስርዓት

ለሞተ ሰው በወኪልነት በሚኖር ሰው የሚከናወን የሀይማኖት ስነስርዓት። እነዚህ ስነስርዓቶች ውጤት የሚኖራቸው ስነስርዓቶች የተከናወኑላቸው ሰዎች ከተቀበሉት፣ ከእነዚህ ጋር የተያያዙትን ቃል ኪዳኖች ከጠበቁ፣ በቅዱስ የተስፋ መንፈስ ከተሳሰሩ በኋላ ብቻ ነው። እንደዚህ አይነት ስነስርዓቶች ዛሬ የሚከናወኑት በቤተመቅደሶች ውስጥ ነው።