እናት ደግሞም ሔዋን; ቤተሰብ; ወላጆች ተመልከቱ ልጆችን ለወለደች ወይም በጉዲፈቻ ለምታሳድግ ሴት የተሰጠ ቅዱስ ስም። እናቶች ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ ልጆች ስጋዊ ሰውነት በመስጠት የእግዚአብሔርን አላማ ይረዳሉ። አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና, ዘፍጥ. ፫፥፳ (ሙሴ ፬፥፳፮). አባትህንና እናትህን አክብር, ዘፀአ. ፳፥፲፪ (ኤፌ. ፮፥፩–፫; ሞዛያ ፲፫፥፳). የእናትህንም ሕግ አትተው, ምሳ. ፩፥፰. ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ይንቃል, ምሳ. ፲፭፥፳ (ምሳ. ፲፥፩). እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት, ምሳ. ፳፫፥፳፪. ልጆችዋ ይነሣሉ፥ ምስጋናዋንም ይናገራሉ፤ ባልዋ ደግሞ እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል, ምሳ. ፴፩፥፳፰. የኢየሱስ እናት በመስቀል አጠገብ ቆመች, ዮሐ. ፲፱፥፳፭–፳፯. ሁለት ሺህ የላማናውያን ጀግናዎች በእናቶቻቸውም ተምረዋል, አልማ ፶፮፥፵፯ (አልማ ፶፯፥፳፩). በእዚህ ታላቅ የጻድቆች ስብሰባ ከተሰበሰቡት ታላቅ እና ሀይለኛ ከሆኑት መካከል የእኛ ግርማዊዋ እናት ሔዋን ነበረች, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፴፰–፴፱.