የክርስቶስ ትምህርት ደግሞም ወንጌል; የቤዛነት ዕቅድ ተመልከቱ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰረታዊ መርሆችና ትምህርቶች። ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትፈስሳለች, ዘዳግ. ፴፪፥፪. የሚያጕረመርሙም ትምህርትን ይቀበላሉ, ኢሳ. ፳፱፥፳፬. ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ, ማቴ. ፯፥፳፰. ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም, ዮሐ. ፯፥፲፮. ቅዱስ መጻሕፍት ሁሉ ለትምህርትና ይጠቅማል, ፪ ጢሞ. ፫፥፲፮. ይህ የክርስቶስ ትምህርት ነው፣ የአብ ብቸኛውና እውነተኛው ትምህርት ነው, ፪ ኔፊ ፴፩፥፳፩ (፪ ኔፊ ፴፪፥፮). በትምህርቴ ነጥቦችም ምክንያት በመካከላችሁ ፀብ አይኖርም, ፫ ኔፊ ፲፩፥፳፰፣ ፴፪፣ ፴፭፣ ፴፱–፵. የትምህርቴ ነጥቦች በተመለከተ ሰይጣን የሰዎችን ልብ ለፀብ ያነሣሳል, ት. እና ቃ. ፲፥፷፪–፷፫፣ ፷፯. ልጆችን ስለንስሀ መግባት፣ በክርስቶስ እምነት፣ እናም ስለጥምቀትና ስለመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ትምህርት አስተምሯቸው, ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፭. የመንግስትን ትምህርቶች እርስ በርስ ተማሩ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፸፯–፸፰. የክህነት ትምህርትም በነፍስህ ላይ እንደ ሰማይ ጠል ይንጠባጠባል, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፵፭.