ዳግመኛ መወለድን፣ ከእግዚአብሔር መወለድ ደግሞም መቀየር፣ የተቀየረ; መወለድ; የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች; የክርስቶስ ልጆች; ጥምቀት፣ መጥመቅ; ፍጥረታዊ ሰው ተመልከቱ የጌታ መንፈስ በሰው ልብ ውስጥ ታላቅ ለውጥ በማምጣት ምንም ክፉ ለማድረግ ፍላጎት ሳይሆን፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ነገሮች ለማድረግ ፍላጎት እንዲኖረው ማድረግ። በውስጣችሁ አዲስ መንፈስ እስገባለሁ, ሕዝ. ፲፩፥፲፱ (ሕዝ. ፲፰፥፴፩; ፴፮፥፳፮). በክርስቶስ ስም የሚያምኑት እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም አልተወለዱም, ዮሐ. ፩፥፲፪–፲፫. ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም, ዮሐ. ፫፥፫–፯. በእግዚአብሔር ቃል እንደገና ለመወለድ እንችላለን, ፩ ጴጥ. ፩፥፫–፳፫. በእግዚአብሔር የተወለደም በኃጢያት አይቀጥልም, ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ዮሐ. ፫፥፱. ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና, ፩ ዮሐ. ፭፥፬. በክርስቶስ የተወለዱ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ይገባሉ, ሞዛያ ፫፥፲፱፤ ፭፥፪–፯. ሁሉም ሰዎች እንደገና መወለድ፣ አዎን በእግዚአብሔር መወለድ አለባቸው, ሞዛያ ፳፯፥፳፭–፳፮ (አልማ ፭፥፵፱). በመንፈስ በእግዚአብሔር የተወለዳችሁ ናችሁ, አልማ ፭፥፲፪–፲፱. በድጋሚ ካልተወለዳችሁ መንግስተ ሰማያትን መውረስ አትችሉም, አልማ ፯፥፲፬. ቃሌን የሚያምኑ ሁሉ…፣ ከእኔም ይወለዳሉ፣ እንዲሁም ከውሃ እና ከመንፈስ, ት. እና ቃ. ፭፥፲፮. ወደ መንግስተ ሰማያት በውሃ፣ በመንፈስ በድጋሚ መወለድ አለብህ, ሙሴ ፮፥፶፱.