የቤተክርስቲያን መሪዎችን መደገፍ ደግሞም የጋራ ስምምነት ተመልከቱ በአጠቃላይ ለሚያገለግሉት እና ለቤተክርስቲያን መሪዎች እርዳታ ለመስጠት ቃል መግባት። ኢያሱን በማኅበሩ ሁሉ ፊት አቁመው፥ እነርሱም እያዩ እዘዘው, ዘኁል. ፳፯፥፲፰–፲፱. ሕዝቡም ሁሉ ንጉሥ ሕያው ይሁን እያሉ እልልታ አደረጉ, ፩ ሳሙ. ፲፥፳፬. በነቢያቱም እመኑ፥ ነገሩም ይሰላላችኋል, ፪ ዜና ፳፥፳. ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ, ዕብ. ፲፫፥፲፯. አንተ ስላላጉረመረምክ በጌታ የተደገፍክ ትሆናለህ, ፩ ኔፊ ፫፥፮. የዳኑትም ነቢያትን የተቀበሉት ናቸው, ፫ ኔፊ ፲፥፲፪–፲፫. እነዚህ አስራ ሁለትን አድምጡ, ፫ ኔፊ ፲፪፥፩. በእኔ ድምጽ ሆነ በአገልጋዮቼ ድምጽ፣ ያም አንድ ነው, ት. እና ቃ. ፩፥፴፰. ቃሉን ልክ ከእኔ አፍ እንደወጣ አድርጋችሁ ትቀበላላችሁ, ት. እና ቃ. ፳፩፥፭. አገልጋዮቼን የሚቀበል፣ እኔን ይቀበላል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፴፭–፴፰. እኔን የሚቀበል፣ የላኳቸውን ይቀበላል, ት. እና ቃ. ፻፲፪፥፳. ህዝቦቼ እነዚህን የመደብኳቸውን ድምፅ ካላዳመጡ፣ አይባረኩም, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፵፭–፵፮.