ስጋዊ፣ የሚሞት ደግሞም ሰውነት; ስጋዊ ሞት; አለም; የአዳም እና የሔዋን ውድቀት ተመልከቱ ከመወለድ እስከ ስጋዊ ሞት ድረስ ያለ ጊዜ። ይህም አንዳንድ ጊዜ ሁለተኛው ሁኔታ ተብሎ ይጠራል። ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ, ዘፍጥ. ፪፥፲፮–፲፯ (ሙሴ ፫፥፲፮–፲፯). ነፍስ ወደ እግዚአብሔር ይመለሳል እናም ሰውነትም አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ይመለሳል, መክ. ፲፪፥፯ (ዘፍጥ. ፫፥፲፱; ሙሴ ፬፥፳፭). በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ, ሮሜ ፮፥፲፪. ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ይለብሳል, ፩ ቆሮ. ፲፭፥፶፫ (ኢኖስ ፩፥፳፯; ሞዛያ ፲፮፥፲; ሞር. ፮፥፳፩). የሰው ዘመን የሙከራ ጊዜ ሆነ, ፪ ኔፊ ፪፥፳፩ (አልማ ፲፪፥፳፬; ፵፪፥፲). ሰዎች እንዲኖሩ፣ አዳም ወደቀ, ፪ ኔፊ ፪፥፳፭. ይህ ሟቹ ሰውነት የማይሞት በመሆን እንደሚነሳ ትመለከታላችሁን, አልማ ፭፥፲፭. ይህ ጊዜ እግዚአብሔርን ለመገናኘት የዝግጅት ወቅት ነው, አልማ ፴፬፥፴፪. እስከሞትም አትፍሩ፤ በዚህ አለም ደስታችሁ ሙሉ አይደለምና, ት. እና ቃ. ፻፩፥፴፮. ሁለተኛ ሁኔታቸውን የጠበቁትም ግርማ ይጨመርላቸዋል, አብር. ፫፥፳፮.