ዳኛ፣ ፍርድ ደግሞም መኮነን፣ ኩነኔ; ኢየሱስ ክርስቶስ—ዳኛ; ፍርድ፣ የመጨረሻው ተመልከቱ ጸባይን በወንጌል መሰረታዊ መርሆች መመዘን፤ መወሰን፤ ጥሩን ከመጥፎ መለየት። ሙሴ በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ, ዘፀአ. ፲፰፥፲፫. ለባልንጀራህ በእውነት ፍረድ, ዘሌዋ. ፲፱፥፲፭. እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ, ማቴ. ፯፥፩ (ጆ.ስ.ት.፣ ማቴ. ፯፥፩–፪; ሉቃ. ፮፥፴፯; ፫ ኔፊ ፲፬፥፩). ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል, ሮሜ ፪፥፲፪. ቅዱሳን በዓለም ላይ ይፈርዳሉ, ፩ ቆሮ. ፮፥፪–፫. የዘለዓለማዊው እግዚአብሔር ልጅ በዓለም ተፈረደበት, ፩ ኔፊ ፲፩፥፴፪. የበጉን አስራ ሁለት ሐዋርያት የእስራኤል አስራ ሁለቱን ነገዶች ይፈርዳሉ, ፩ ኔፊ ፲፪፥፱ (ት. እና ቃ. ፳፱፥፲፪). ሞት፣ ሲኦል፣ ዲያብሎስና በእነርሱም የተያዙት ሁሉ ይፈረድባቸዋል, ፪ ኔፊ ፳፰፥፳፫ (፩ ኔፊ ፲፭፥፴፫). አንድ ሰው ካላችሁ ሀብት እንድታካፍሉት የሚጠይቃችሁን ከፈረዳችሁበት፣ ሀብታችሁን በመያዛችሁ ኩነኔያችሁም ምን ያህል ትክክል ይሆናል, ሞዛያ ፬፥፳፪. ሰዎች እንደስራቸው ይፈረድባቸዋል, አልማ ፵፩፥፫. በትክክል ፍረድ፣ በድጋሚም ፍትህ ይመለስልሃል, አልማ ፵፩፥፲፬. ከሚፃፉት መጽሐፍት ይህ ህዝብ ይፈረድበታል, ፫ ኔፊ ፳፯፥፳፫–፳፮ (ራዕ. ፳፥፲፪). በዚህች ምድር ኢየሱስ በመረጣቸው በአስራ ሁለቱ የሕዝቦች ቅሪት ይፈረድባቸዋል, ሞር. ፫፥፲፰–፳. ሞርሞን ጥሩን ከመጥፎ የሚፈረድበትን መንገድ ገለጸ, ሞሮኒ ፯፥፲፬–፲፰. ወደ መልካም በሚመራው መንፈስ ላይ እምነትህን አድርግ, ት. እና ቃ. ፲፩፥፲፪. በልባችሁም እንዲህ ማለት ይገባችኋል—በእኔ እና በአንተ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ, ት. እና ቃ. ፷፬፥፲፩. የጌታ ቤተክርስቲያን አገሮችን ትፈርዳለች, ት. እና ቃ. ፷፬፥፴፯–፴፰. እንደሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው ዘንድ ወልድ በወኀኒ ውስጥ የነበሩት የሰዎች ነፍሶች ጎበኛቸው, ት. እና ቃ. ፸፮፥፸፫ (፩ ጴጥ. ፬፥፮). ኤጲስ ቆጶስ ዳኛ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፻፯፥፸፪–፸፬. ጌታ ሁሉንም ሰዎች በስራዎቻቸው መሰረት፣ በልቦቻቸው ፍላጎት መሰረት ይፈርድባቸዋል, ት. እና ቃ. ፻፴፯፥፱.