የመለየት ስጦታ ደግሞም የመንፈስ ስጦታዎች ተመልከቱ ማስተዋል ወይም አንድ ነገርን በመንፈስ ሀይል ማወቅ። የመለየት ስጦታ ከመንፈስ ስጦታዎች አንዱ ነው። ይህም የሰዎችን እውነተኛ ጸባይ እና በመንፈስ መታየትን ምንጭና ትርጉምን ለይቶ የማወቅን ችሎታ ይጨምራል። ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል, ፩ ሳሙ. ፲፮፥፯. ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ ወዮላቸው, ኢሳ. ፭፥፳ (፪ ኔፊ ፲፭፥፳). የእግዚአብሔር ነገር በመንፈስ የሚመረመር ነው, ፩ ቆሮ. ፪፥፲፬. ለአንዱም መናፍስትን የመለየት ስጦታ ተስጥቷል, ፩ ቆሮ. ፲፪፥፲. አሞን ሀሳቡን ለመረዳት ችሏል, አልማ ፲፰፥፲፰. ድምፁ አነስተኛ ቢሆንም እንኳን የሰሙት ውስጣቸውን ሰንጥቆ ገብቶ, ፫ ኔፊ ፲፩፥፫. እንዳትታለሉ፣ ከሁሉም የሚበልጡትን ስጦታዎች ፈልጉ, ት. እና ቃ. ፵፮፥፰፣ ፳፫. የቤተክርቲያኗ መሪዎች የመንፈስ ስጦታዎችን ለይተው እንዲያውቁ ተሰጥቷቸዋል, ት. እና ቃ. ፵፮፥፳፯. ብሩህ የሆነ ሰውነትም ሁሉንም ነገሮች ይረዳል, ት. እና ቃ. ፹፰፥፷፯. ሙሴ ምድርን አየ፤ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ለይቶ አወቀ, ሙሴ ፩፥፳፯.