የጥናት እርዳታዎች
እስራኤል


እስራኤል

በብሉይ ኪዳን ውስጥ ጌታ የእስራኤልን ስም ለይስሐቅ ልጅ እና ለአብርሐም የልጅ ልጅ ያዕቆብ ሰጠው (ዘፍጥ. ፴፪፥፳፰፴፭፥፲)። የእስራኤል ስም ያዕቆብን፣ ትውልዶቹን፣ ወይም በብሉይ ኪዳን ዘመናት እነዚያ ትውልዶች የነበራቸውን መንግስት ለመጠቆም የሚቻል ነው። (፪ ሳሙ. ፩፥፳፬፳፫፥፫)። ሙሴ የእስራኤል ልጆችን ከግብፅ ባርነት መርቶ ካስወጣ በኋላ (ዘፀአ. ፫–፲፬)፣ ለሶስት መቶ አመታት በመሳፍንት ተመርተው ነበር። ከንጉስ ሳኦል ጀምሮ፣ ንጉሶች አንድ የነበረችውን እስራኤል አስሩ ጎሳዎች ከሮብዓም በማመፅ የተለያየ ሀገር እስከ መሰረቱበት እስከ ሰለሞን ሞት ድረስ ገዙ። የእስራኤል መንግስት ከተከፋፈለ በኋላ፣ የሰሜን ጎሳዎች እንደ ትልቅነታቸው የእስራኤልን ስም ጠበቁ፣ የደቡብ መንግስት ግን ጅሁዳ ተብሎ ተጠራ። የከነዓን ምድርም ዛሬ እስራኤል ተብሎ ይጠራል። በሌላ አባባል፣ እስራኤል ማለት እውነተኛ የክርስቶስ ታማኞች ናቸው (ሮሜ ፲፥፩፲፩፥፯ገላ. ፮፥፲፮ኤፌ. ፪፥፲፪)።

የእስራኤል አስራ ሁለት ጎሳዎች

ስሙ ወደ እስራኤል የተቀየረው የአብርሐም የልጅ ልጅ ያዕቆብ አስራ ሁለት ልጆች ነበሩት። የእነርሱም ትውልዶች የእስራኤል አስራ ጎሳዎች ወይም የእስራኤል ልጆች ተብለው ተጠርተዋል። አስራ ሁለቱ ጎሳዎች እነዚህ ናቸው፥ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ እና ዛብሎን (የያዕቆብ እና የልያ ወንድ ልጆች)፤ ዳን እና ንፍታሌም (የያዕቆብ እና የባላ ወንድ ልጆች)፤ ጋድ እና አሴር (የያዕቆብ እና የዘልፋ ወንድ ልጆች)፤ ዮሴፍ እና ቢንያም (የያዕቆብ እና የራሔል ወንድ ልጆች) (ዘፍጥ. ፳፱፥፴፪–፴፥፳፬፴፭፥፲፮–፲፰)።

ያዕቆብ ለእያንዳንዱ የጎሳ መሪ ከመሞቱ በፊት በረከት ሰጠ (ዘፍጥ. ፵፱፥፩–፳፰)። ለዚህ ተጨማሪ ማስረጃ፣ የእያንዳንዱን የያዕቆብን ልጆች ስም ተመልከቱ።

የያዕቆብ የመጀመሪያ ባለቤት ልያ የበኩር ልጅ ሮቤል የበኩር በረከቱን እና የውርሱን ሁለት እጥፍ በስነ ምግባር ጉድለት አጣ (ዘፍጥ. ፵፱፥፫–፬)። ከእዚያም በኩርነትም ወደ ያዕቆብ ሁለተኛ ባለቤት ራሔል የበኩር ልጅ ዮሴፍ ሄደ(፩ ዜና ፭፥፩–፪)። ጎሳው እንደ ክህነት ስልጣን አገልጋዮች ለማገልገል የመረጡት ሌዊ በጎሳዎች ሁሉ መካከል ለማገልገል በነበራቸው ልዩ ጥሪ ምክንያት ውርስን አልተቀበለም። ይህም የዮሴፍ ሁለት እጥፍ ክፍል እንደተለያዩ ጎሳዎች በተቆጠሩት (ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥ. ፵፰፥፭–፮ [ተጨማሪ]) በዮሴፍ ልጆች በኤፍሬም እና በምናሴ መካከል ተከፋፈለ። (፩ ዜና ፭፥፩ኤር. ፴፩፥፱)።

የይሁዳ ጎሳዎች አባላት መሲህ እስከሚመጣ ድረስ ገዢዎች ነበሩ (ዘፍጥ. ፵፱፥፲ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥ. ፶፥፳፬)። በመጨረሻው ቀናት የኤፍሬም ጎሳ ዳግም የተመለሰውን ወንጌል ወደ አለም ለመውሰድ እና የተበተኑትን እስራኤል የመሰብሰብ እድል አላቸው (ዘዳግ. ፴፫፥፲፫–፲፯)። በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ኤፍሬም የእስራኤል ጎሳዎችን አንድ ለማድረግ የመሪነት ሀላፊነት የሚኖርበት ጊዜ ይመጣል (ኢሳ. ፲፩፥፲፪–፲፫ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፳፮–፴፬)።

የተበተኑት እስራኤል

ጌታ አስራ ሁለቱ ጎሳዎችን ጻድቅ ባለመሆናቸውና በማመጻቸው ምክንያት በተናቸው እናም አሰቃያቸው። ነገር ግን፣ ጌታ ይህን የተመረጡትን ህዝቦቹን በአለም ሀገሮች መካከል በመበተን እነዚያን ሀገሮች ለመባረክ ተጠቀመበት።

የእስራኤል መሰብሰብ

የእስራኤል ቤት ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በመጨረሻው ቀን አብረው ይሰበሰባሉ (እ.አ. ፩፥፲)። ጌታ ህዝቡ እስራኤልን በሚቀበሉት ጊዜ እና ትእዛዛቱን ሲያከብሩ ይሰበስባቸዋል።

የጠፉት የእስራኤል አስር ጎሳዎች

የእስራኤል አስር ጎሳዎች የሰሜን የእስራኤል መንግስት የሰሩ ነበሩ እናም በ፯፻፲፪ ም.ዓ. በአሶር በምርኮ ተወሰዱ። በእዚያ ጊዜ ወደ “ሰሜን ሀገሮች ሄዱ” እናም ከሌሎች እውቀቶችም ጠፉ። በመጨረሻው ቀናትም ይመለሳሉ።