ተስፋ ደግሞም እምነት፣ ማመን ተመልከቱ ቃል ለተገቡት የጽድቅ በረከቶች በልበ ሙሉነት መጠበቅ እና በጉጉት መመኘት። ቅዱሣት መጻህፍት ብዙ ጊዜ ተስፋ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት በኩል የዘለአለም ህይወትን መጠበቅ እንደሆነ ይናገራሉ። እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው, ኤር. ፲፯፥፯. እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ ይሆናል, ኢዩ. ፫፥፲፮. በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ አለን, ሮሜ ፲፭፥፬. ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋ ሰጥቶናል, ፩ ጴጥ. ፩፥፫. ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል, ፩ ዮሐ. ፫፥፪–፫. ፍጹም የሆነ የተስፋ ብርሃን እየኖራችሁ መቀጠል አለባችሁ፣ አሜን, ፪ ኔፊ ፴፩፥፳. እምነት፣ ተስፋና ልግስና እንደሚኖራችሁ እርግጠኛ ሁኑ, አልማ ፯፥፳፬ (፩ ቆሮ. ፲፫፥፲፫; ሞሮኒ ፲፥፳). ዘለአለማዊ ህይወትን ለመቀበል በተስፋ የተሞላችሁ ሁኑ, አልማ ፲፫፥፳፯–፳፱. እምነት ካላችሁ እውነት ስለሆኑትና ስለማይታዩት ነገሮች ተስፋ ይኖራችኋል, አልማ ፴፪፥፳፩ (ዕብ. ፲፩፥፩). ተስፋ በእምነት የሚመጣ ነው፤ ተስፋም ለሰዎች ነፍስ እንደመሃልቅ ነው, ኤተር ፲፪፥፬ (ዕብ. ፮፥፲፯–፲፱). ሰው ተስፋ ማድረግ ይገባዋል፣ አለበለዚያ ውርስን ሊቀበል አይችልም, ኤተር ፲፪፥፴፪. ሞርሞን ስለእምነት፤ ተስፋ እና ልግስና ተናገረ, ሞሮኒ ፯፥፩. በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ለዘለዓለም ህይወት እንዲኖራችሁ ተስፋ ይኑራችሁ, ሞሮኒ ፯፥፵–፵፫. መንፈስ ቅዱስ በተስፋ ይሞላል, ሞሮኒ ፰፥፳፮ (ሮሜ ፲፭፥፲፫). ለግርማዊ ትንሳኤ ፅኑ ተስፋ ኖሮአቸው ከስጋ ህይወት ሄደው ነበር, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፲፬.