ሰባ ደግሞም ሐዋሪያ; የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተመልከቱ በመልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ ወንዶች ሊሾሙበት የሚችሉ ሀላፊነት። ዛሬ፣ የሰባ ቡድኖች የቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ባለስልጣኖች እና የክልል አመራሮች ናቸው። ሰባዎች በቀዳሚ አመራር እና በአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን አመራር ስር በጌታ ስም ያገለግላሉ (ት. እና ቃ. ፻፯፥፴፬)። ሙሉ ጊዜአቸውን ለማስተማር ይሰጣሉ። ከጌታ ሌሎቹን ሰብዓ ሾመ, ሉቃ. ፲፥፩. ሰባዎቹ ወንጌልን እንዲሰብኩ፣ እና ልዩ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች እንዲሆኑ ተጠርተዋል, ት. እና ቃ. ፻፯፥፳፭–፳፮. ሰባዎች፣ በአስራ ሁለቱ አመራር በኩል ቤተክርስቲያኗን በመገንባት እና የእርሷን ጉዳዮች በሀገሮች ውስጥ ሁሉ በመቆጣጠር በጌታ ስም ሰሩ, ት. እና ቃ. ፻፯፥፴፬. ስራው የሚያስፈልገው ከሆነ ሌሎች ሰባዎች፣ እንዲሁን ሰባት ጊዜ ሰባ፣ ምረጥ, ት. እና ቃ. ፻፯፥፺፫–፺፯. የሰባዎች ቡድን የተመሰረተው የሚጓዙ ሽማግሌዎች በአለም ሁሉ ስለ ስሜ እንዲመሰክሩ ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፻፴፰–፻፴፱.