ሞዛያ፣ የቢንያም ልጅ
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የኔፋውያን ጻድቅ ንጉስ እና ነቢይ። ሞዛያ የአባቱን ጻድቅ ምሳሌ ተከተለ (ሞዛያ ፮፥፬–፯)። የያሬዳውያን መዝገቦችን የያዙትን ሀያ አራት የወርቅ ሰሌዳዎች ተረጎመ (ሞዛያ ፳፰፥፲፯)።
መፅሐፈ ሞዛያ
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኝ መፅሐፍ። ምዕራፍ ፩–፮ ንጉስ ቢንያም ለሕዝቡ የሰጠውን ሀይለኛ ስብከት የያዙ ናቸው። የጌታ መንፈስ ልባቸውን ነካቸው እና ህዝቡም ተቀየሩ፣ እንዲሁም ክፉ ለማድረግ ምንም ፍላጎት አይሰማቸውም። ምዕራፍ ፯–፰ በላማናውያን ምድር ለመኖር ስለሄዱ የኔፋውያን ቡድን ይናገራሉ። የሚፈልጓቸው ቡድን ተልከው ነበር። የሚፈልጉት ቡድን መሪ አሞን አገኛቸው እናም በላማናውያን ጭቆና ስር ስለነበራቸው ፈተናዎች ታሪክ ተማረ። ምዕራፍ ፱–፳፬ ያን ጭቆና እና እንዴት መሪአዎቻቸው ዜኒፍ፣ ኖኅ፣ እና ሊምሂ በላማናውያን ስር እንደኖሩ ይገልጻሉ። አቢናዲ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ ሰማዕትም ተመዝግቧል። አልማ አቢናዲ ለፍርድ በቀረበበት ጊዜ ተቀየረ። ምዕራፍ ፳፭–፳፰ የአልማ ልጅ እና የንጉስ ሞዛያ አራት ልጆች እንዴት እንደተቀየሩ ታሪክን ይነግራሉ። በምዕራፍ ፳፱ ውስጥ ንጉስ ሞዛያ የመሳፍንት መንግስት ንጉሶችን እንዲተኩ ሀሳብ አቀረበ። የአልማ ልጅ አልማ ዋና ዳኛ እንዲሆን ተመረጠ።