ሟች አባት ደግሞም ቤተሰብ; ወላጆች; የአባቶች አለቃ፣ ፓትሪያርክ; የፓትሪያርክ በረከቶች ተመልከት ልጅን ለወለደ ወይም በጉዲፈቻ ላሳደገ ሰው የሚሰጥ ቅዱስ ርዕስ። አባትህንና እናትህን አክብር, ዘፀአ. ፳፥፲፪ (ዘዳግ. ፭፥፲፮; ማቴ. ፲፱፥፲፱; ሞዛያ ፲፫፥፳). አባት የሚወደውን ልጁን እንደሚገሥጽ, ምሳ. ፫፥፲፪. አባቶች ሆይ፥ አታስቆጡአቸው, ኤፌ. ፮፥፩–፬. አባቴ ከሚያውቃቸው በመጠኑ ተማርኩ, ፩ ኔፊ ፩፥፩. አባቴ ፃድቅ ሰው ነበር—አስተማሮኛልና, ኢኖስ ፩፥፩. አልማ ለልጁ ጸለየ, ሞዛያ ፳፯፥፲፬. አልማ ለልጆቹ ትእዛዛትን ሰጠ, አልማ ፴፮–፵፪. ሔለመን ልጆቹን የቅድመ አያቶቹን ስም ሰጣቸው, ሔለ. ፭፥፭–፲፪. ሞርሞን ልጁን በጸሎቱ ሁልጊዜ ያስታውሳል, ሞሮኒ ፰፥፪–፫. ታላላቅ ነገሮች ከአባቶቻቸው እጅ ይጠበቃል, ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፰. ቤተሰቡን የማስተዳደር ሀላፊነት እያንዳንዱም ሰው አለበት, ት. እና ቃ. ፸፭፥፳፰. ወደ አባቴ እንድሄድ አዘዘኝ, ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፵፱.