የጥናት እርዳታዎች
የመጀመሪያው ራዕይ


የመጀመሪያው ራዕይ

እግዚአብሔር አብ እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በጥሻ ውስጥ የታዩበት።

በጸደይ ፲፰፻፳ (እ.አ.አ.) ውስጥ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ አስራ አምስት አመቱ ነበር። በፓልማይራ፣ ኒው ዮርክ ከተማ፣ ውስጥ ከቤተሰቡ ጋር ይኖር ነበር። ከቤተሰቡ ቤት በስተምዕራብ በኩል የትትልቅ ዛፎች ጥሻ ነበር። ጆሴፍ ወደዚህ ቦታ የትኛው ቤተክርስቲያን ትክክል እንደሆነ ለእግዚአብሔር ለመጸለይ ሄደ። መፅሐፈ ሞርሞንን እያነበበ እያለ መልሱን ከእግዚአብሔር መፈለግ እንዳለበት ተነሳስቶ ነበር (ያዕ. ፩፥፭–፮)። ለጸሎቱ መልስ፣ አብና ወልድ ለእርሱ ታዩት እናም በእዚያ ጊዜ በምድር ላይ የነበሩትን ማንኛውንም ቤተክርስቲያናት አባል እንዳይሆን ነገሩት፣ ሁሉም የተሳሳቱ ነበሩና (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፲፭–፳)። ይህም ቅዱስ አጋጣሚ የወንጌሉን እና የክርስቶስ እውነተኛ ቤተክርስቲያን ዳግም መመለስ ያመጣ የተከታተሉ ድርጊቶችን ጀመረ።