ማሰላሰል ደግሞም ራዕይ; ጸሎት ተመልከቱ በቅዱስ መጻህፍቶች እና በሌሎች የእግዚአብሔር ነገሮች መመሰጥ እና በጥልቅ ማሰብ። ከጸሎት ጋር ሲጣመር፣ የእግዚአብሔር ነገሮችን ማሰላሰል ራዕይን እና ማስተዋልን ያመጣል። ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር, ሉቃ. ፪፥፲፱. በልቤ እያሰላሰልኩ ተቀምጬ ሳለሁ ተወሰድኩ, ፩ ኔፊ ፲፩፥፩. ልቤ ታሰላስላቸዋለች, ፪ ኔፊ ፬፥፲፭. ኔፊ ጌታ ያሳየውን ነገሮች በልቡ እያሰላሰለ ወደ ራሱ ቤት መንገዱን አቀና, ሔለ. ፲፥፪–፫. ወደ ቤታችሁ ሂዱ፣ እናም ስለተናገርኳችሁ ነገሮች አሰላስሉ, ፫ ኔፊ ፲፯፥፫. ጌታ ምን ያህል መሃሪ እንደነበረ አስታውሱ፣ እናም በልባችሁ ይህን አሰላስሉ, ሞሮኒ ፲፥፫. ስለተቀብልካቸው ነገሮች አሰላስል, ት. እና ቃ. ፴፥፫. እነዚህ ነገሮች ላይ እያሰላሰልን እያለን፣ ጌታ የመረጃ አይኖቻችንን ነካን, ት. እና ቃ. ፸፮፥፲፱. በቅዱሣት መጻህፍት ላይ በክፍሌ ቁጭ ብዬ አሰላስል ነበር, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፩–፲፩. ይህን ደጋግሜ አሰብኩበት, ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፲፪.