መፅሐፈ ነገሥት
በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙ ሁለት መፅሐፎች። እነዚህ መፅሐፎች ከንጉስ ዳዊት አራተኛ ወንድ ልጅ ከአዶንያስ አመጽ (በ፲፻፲፭ ም.ዓ. አካባቢ) እስከ ይሁዳ መጨረሻ ምርኮ ድረስ (፭፻፹፮ ም.ዓ. አካባቢ) የእስራኤል ታሪክን ይዘረዝራሉ። እነዚህም ከተለያዩበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሰሜን አገሮች ሶርያዎች በምርኮ እስከሚወስዷቸው ድረስ የሰሜን መንግስት (የእስራኤል አስር ጎሳዎች) ታሪኮችን በሙሉ ጨምረው ይዘረዝራሉ። ደግሞም የዘመን ቅድመ ተከተል በተጨማሪ ውስጥ ተመልከቱ።
መፅሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
ምዕራፍ ፩ የንጉስ ዳዊት የመጨረሻ ቀናትን ገልጿል። ምዕራፍ ፪–፲፩ የሰለሞን ህይወትን መዝግበዋል። ምዕራፍ ፲፪–፲፮ ስለሰለሞን ወራሾች፣ ሮብዓም እና ኢዮርብዓም ተናግረዋል። ኢዮርብዓም የእስራኤል መንግስት መከፋፈል ምክንያት ነበር። ደግሞም ሌሎች ንጉሶችም ተጠቅሰዋል። ምዕራፍ ፲፯–፳፩ የኤልያስ አገልግሎት ክፍልን፣ የእስራኤል ንጉስ አክዓብ ሲገስጽ፣ መዝግበዋል። ምዕራፍ ፳፪ አክዓብ እና የእስራኤል ንጉስ ኢዮሣፍጥ ሀይላቸውን አንድ ያደረጉበትን ከሶሪያ ጋር ጦርነትን መዝግቧል። ነቢዩ ሚክያስ ንጉሶችን በመቃወም ተነበየ።
መፅሐፈ ነገሥት ካልዕ
ምዕራፍ ፩፥፩–፪፥፲፩ የኢልያስን ህይወት፣ በተጨማሪም በእሳት ሰረገላ ወደሰማይ ያረገበትን፣ ታሪክ ቀጥለዋል። ምዕራፍ ፪–፱ የኤልሳዕን የእምነት እና የታላቅ ሀይል አገልግሎትን ተናግረዋል። ምዕራፍ ፲ ስለንጉሱ ኢዩ እና የአክዓብ ቤትን እና የብዔል ቄሶችን እንዴት እንዳጠፋ ተናግሯል። ምዕራፍ ፲፩–፲፫ የኢዮአስምን ጻድግ ዘመነ መንግስት እና የኤልሳዕን ሞት መዝግበዋል። ምዕራፍ ፲፬–፲፯ በእስራኤል እና በይሁዳ ውስጥ፣ በብዙ ጊዜ በኃጢያተኛነት፣ ስለነገሱ የተለያዩ ንጉሶች ተናግረዋል። ምዕራፍ ፲፭ አሶር የእስራኤል አስር ጎሳዎችን ስለመማረካቸው መዝግቧል። ምዕራፍ ፲፰–፳ የይሁዳ ንጉስ የሕዝቅያስን እና የነቢዩ ኢሳይያስን ጻድቅ ህይወት መዝግቧል። ምዕራፍ ፳፩–፳፫ ስለንጉሶች ምናሴና ኢዮስያስ ተናግረዋል። በባህል መሰረት፣ ምናሴ ለኢሳይያስ ሰማዕት ሀላፊ ነበር። ኢዮስያስ በአይሁዳ መካከል ህግን የመሰረተ ጻድቅ ንጉስ ነበር። ምዕራፍ ፳፬–፳፭ ስለባቢሎን ምርኮ መዝግበዋል።