ፕሬዘደንት
ለድርጅት መሪ ሀላፊነት የተሰጠ ርዕስ። የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ነቢይ፣ ባለራዕይ፣ እና ገላጭ ነው (ት. እና ቃ. ፳፩፥፩፤ ፻፯፥፺፩–፺፪)፣ እናም የቤተክርስቲያኗ አባላት የቤተክርስቲያኗን ነቢይ “በፕሬዘደንት” ርዕስ ይጠሯቸዋል (ት. እና ቃ. ፻፯፥፷፭)። እርሱ ብቻ የክህነት ቆልፎችን በሙሉ ለመጠቀም በምድር ላይ ስልጣን ያለው ሰው ነው።
የክህነት ቡድን እና የሌሎች የቤተክርስቲያን ድርጅቶች መሪ የፕሬዘደንት ርዕስ ሊኖራቸው ይችላሉ።