ትሁት፣ ትሕትና ደግሞም ኩራት; የተሰበረ ልብ; ደሀ; ደካማነት; ገር፣ ገርነት ተመልከቱ የዋህ እና ለማስተማር የሚቻል ማድረግ፣ ወይም የዋህ እና ለማስተማር የሚቻል የመሆን ጉዳይ። ትህትና በእግዚአብሔር እንደምንመካ ማወቅን እና ለእርሱ ፍላጎት ተቀባይ ለመሆን መፈለግን በተጨማሪ ይይዛል። አምላክህ እግዚአብሔር ሊያስጨንቅህ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ መራህን, ዘዳግ. ፰፥፪. ነፍሴንም በጾም አደከምኋት, መዝ. ፴፭፥፲፫. ድሀና ጠቢብ ብላቴና ከማያውቅ ከሰነፍ ሽማግሌ ንጉሥ ይሻላል, መክ. ፬፥፲፫. ጌታ የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር ይቀመጣል, ኢሳ. ፶፯፥፲፭. እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው, ማቴ. ፲፰፥፬. ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል, ማቴ. ፳፫፥፲፪ (ሉቃ. ፲፬፥፲፩; ፲፰፥፲፬). ኢየሱስ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም እንኳ የታዘዘ ሆነ, ፊልጵ. ፪፥፰ (ሉቃ. ፳፪፥፵፪; ፳፫፥፵፮). እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል, ፩ ጴጥ. ፭፥፭–፮ (፪ ኔፊ ፱፥፵፪). በመቆም በጥልቅ ትህትና እንኳን ራሳችሁን አዋርዱ, ሞዛያ ፬፥፲፩ (፪ ኔፊ ፱፥፵፪; ፫ ኔፊ ፲፪፥፪). በሚገባ ትሁት ናችሁ, አልማ ፭፥፳፯–፳፰. ትሁት የሆኑት በትህትና እየጠነከሩ ሄዱ, ሔለ. ፫፥፴፫–፴፭. ሰዎች ትሁት እንዲሆኑ ድካምን እሰጣቸዋለሁ, ኤተር ፲፪፥፳፯. ትሁትነት ለጥምቀት ብቁ የሚያደርግ ነው, ት. እና ቃ. ፳፥፴፯. በፊቴ ትሁት ከሆናችሁ፣ መጋረጃውም ይገፈፋል እናም አይታችሁኝ እኔ ማን እንደሆንኩም ታውቃላችሁ, ት. እና ቃ. ፷፯፥፲. ትሁት ሁን፤ እና ጌታ ለጸሎቶችህም መልስ ይሰጥሀል, ት. እና ቃ. ፻፲፪፥፲. ደንቆሮው እራሱን ትሁት በማድረግ ጥበብን ይማር, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፴፪. ትሁቱን ለማስረዳት መንፈስ ተልኳል, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፴፫.