ደካማነት ደግሞም ትሁት፣ ትሕትና ተመልከቱ ስጋዊ መሆን እናም ችሎታ፣ ጥንካሬ፣ ወይም ብቃት ማጣት። ደካማነት የመሆን ሁኔታ ነው። ሁሉም ሰዎች ደካማ ናቸው፣ እናም ጻድቅ ስራ ለመስራት ሀይል የሚቀበሉት በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው (ያዕቆ. ፬፥፮–፯)። ይህም ደካማነት የሚታየው በክፍል በግለሰብ ደካማነት ወይም እያንዳንዱ ሰው ባለው የጥንካሬ ደካማነት ነው። የደከሙትን እጆች አበርቱ, ኢሳ. ፴፭፥፫–፬. መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው, ማቴ. ፳፮፥፵፩ (ማር. ፲፬፥፴፰). በስጋ መሰረት በውስጤ ባለው ደካማነት ራሴ አመካኛለሁ, ፩ ኔፊ ፲፱፥፮. ምንም እንኳን ደካማ ብሆንም እነዚህን ነገሮች እንድፅፍ በእርሱ ታዘዝኩ, ፪ ኔፊ ፴፫፥፲፩. አገልጋይህ በፊትህ ደካማ በመሆኑ አትቆጣው, ኤተር ፫፥፪. ስንፅፍ ደካሞች በመሆናችን አህዛብ ይሳለቁብናል, ኤተር ፲፪፥፳፫–፳፭፣ ፵. ድካማቸውን አሳያቸዋለሁ, ኤተር ፲፪፥፳፯–፳፰. ድካምህን በማየትህ ጠንካራ ትደረጋለህ, ኤተር ፲፪፥፴፯. ከዚህ በኋላ ከእናንተ መካከል ደካማ የሆነውም ጠንካራ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፶፥፲፮. ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ድክመትን ያውቃል, ት. እና ቃ. ፷፪፥፩.