ዳን
በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የያዕቆብና የራሔል ገረድ የባላ ልጅ (ዘፍጥ. ፴፥፭–፮)።
የዳን ጎሳ
ያዕቆብ ለዳን የሰጠውን በረከት ለማየት፣ ዘፍጥ. ፵፱፥፲፮–፲፰ ተመልከቱ። ሙሴ ለዳን ጎሳዎች የሰጠውን በረከቶች ለማየት፣ ዘዳግ. ፴፫፥፳፪ ተመልከቱ። በከነዓን ከሰፈሩ በኋላ፣ የዳን ጎሳዎች ትንሽ ግን በጣም የለማች መሬት ተሰጣቸው (ኢያ. ፲፱፥፵–፵፰)። ከአሞራውያን (መሳ. ፩፥፴፬) እና ከፍልስጤማውያን (መሳ. ፲፫፥፪፣ ፳፭፤ ፲፰፥፩) ይህን ለመከላከል ታላቅ ችግር ነበራቸው። በዚህም ምክንያት፣ ዳናውያን ወደ ሰሜን ፍልስጤም (መሳ. ፲፰)፣ በሌሳ አካባቢ ሄዱ፣ ከተማውንም ዳን ብለው ጠሩት። ይህም “ከዳን ወደ ቤርሳቤህ” የተዘረጋ በደንብ የታወቀ የፍልስጤም የሰሜን ከተማ ወሰን ነው።