ትንሳኤ
ከሞት በኋላ የመንፈስ ሰውነት ስጋ እና አጥንት ካለው ከስጋዊ ሰውነት ጋር እንደገና መገናኘት። ከትንሳኤ በኋላ፣ መንፈስ እና ሰውነት እንደገናም አይለያዩም፣ እናም ሰውም የማይሞት ይሆናል። በምድር ላይ የተወለደ ሰው በሙሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ሞትን ያሸንፋል (፩ ቆሮ. ፲፭፥፳–፳፪)።
ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ከሞት ለመነሳት የመጀመሪያው ነበር (የሐዋ. ፳፮፥፳፫፤ ቄላ. ፩፥፲፰፤ ራዕ. ፩፥፭)። አዲስ ኪዳን ኢየሱስ በስጋዊ ሰውነቱ እንደተነሳ ብዙ መረጃዎችን ይሰጣል፥ መቃብሩ ባዶ ነበር፣ አሳ እና ማር በላ፣ የስጋ እና አጥንት ሰውነት ነበረው፣ ሰዎች ነኩት፣ እና መላእክት ተነስቷል አሉ (ማር. ፲፮፥፩–፮፤ ሉቃ. ፳፬፥፩–፲፪፣ ፴፮–፵፫፤ ዮሐ. ፳፥፩–፲፰)። የኋለኛው ቀን ራዕይ የክርስቶስና የሰው ዘር ሁሉ ትንሳኤን እውነተኛነት አረጋገጠ (አልማ ፲፩፥፵–፵፭፤ ፵፤ ፫ ኔፊ ፲፩፥፩–፲፯፤ ት. እና ቃ. ፸፮፤ ሙሴ ፯፥፷፪)።
ሁሉም ሰዎች ወደ አንድ አይነት ክብር ከሞት አይነሱም (፩ ቆሮ. ፲፭፥፴፱–፵፪፤ ት. እና ቃ. ፸፮፥፹፱–፺፰)፣ ወይም በአንድ ጊዜ ሁሉም ከሞት አይነሱም (፩ ቆሮ. ፲፭፥፳፪–፳፫፤ አልማ ፵፥፰፤ ት. እና ቃ. ፸፮፥፷፬–፷፭፣ ፹፭፤ ፹፰፥፺፮–፻፪)። ብዙ ቅዱሳን ከክርስቶስ ትንሳኤ በኋላ ከሞት ተነስተው ነበር (ማቴ. ፳፯፥፶፪)። ጻድቃን ከኃጢያተኞች በፊት ከሞት ይነሳሉ እናም በመጀመሪያው ትንሳኤ ይመጣሉ (፩ ተሰ. ፬፥፲፮)፤ ንስሀ ያልገቡት ኃጢያተኞች በመጨረሻው ትንሳኤ ይመጣሉ (ራዕ. ፳፥፭–፲፫፤ ት. እና ቃ. ፸፮፥፹፭)።