የጥናት እርዳታዎች
ሀሪስ፣ ማርቲን


ሀሪስ፣ ማርቲን

ስለመፅሐፈ ሞርሞን መለኮታዊ ስነ ነገርነት እና እውነተኛነት ምስክር ከሆኑት ከሶስት አንዱ። ለጆሴፍ ስሚዝን እና ለቤተክርስቲያኗን በገንዘብ እርዳታ ሰጠ። ጌታ ማርቲን ሀርስን ንብረቱን እንዲሸጥ እና ገንዘቡን መፅሐፈ ሞርሞንን ለማተም እንዲሰጥ (ት. እና ቃ. ፲፱፥፳፮–፳፯፣ ፴፬–፴፭)፣ ለቤተክርስቲያኗ ምሳሌ እንዲሆን (ት. እና ቃ. ፶፰፥፴፭)፣ እና የአገልግሎትን ወጪ እንዲከፍል ጠየቀው (ት. እና ቃ. ፻፬፥፳፮)።

ማርቲን ሀርስ ከቤተክርስቲያኗ ተወገዘ ነገር ግን በኋላም ወደ ሙሉ አባልነት ተመለሰ። እስከ ህይወቱ መጨረሻ ድረስ መልአኩ ሞሮኒን እና ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን የተረጎመበትን የወርቅ ሰሌዳዎችን እንዳየ መሰክሯል።