ህልም ደግሞም ራዕይ ተመልከቱ በምድር ላይ እግዚአብሔር ፈቃዱን ለወንዶችና ለሴቶች የሚሰጥበት አንድ መንገድ። ነገር ግን፣ ሁሉም ህልሞች ራዕዮች አይደሉም። የተነሳሱ ህልሞች የእምነት ፍሬ ናቸው። ህልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል ሰማይ ደርሶ ነበር, ዘፍጥ. ፳፰፥፲፪. ዮሴፍም ህልምን አለመ, ዘፍጥ. ፴፯፥፭. ጌታ በራዕይ ይገልጥለታል, ዘኁል. ፲፪፥፮. ናቡከደነዖር ህልምን አለመ, ዳን. ፪፥፩–፫. ሽማግሌዎቻችሁም ህልምን ያልማሉ, ኢዩ. ፪፥፳፰ (የሐዋ. ፪፥፲፯). የጌታ መልአክ በሕልም ታየው, ማቴ. ፩፥፳ (ማቴ. ፪፥፲፱). ሌሂ በህልም ያያቸውን ብዙ ነገሮች ፅፏል, ፩ ኔፊ ፩፥፲፮. ሌሂ ህልምን አለመ, ፩ ኔፊ ፰.