ሌዊ
በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የያዕቆብ እና የልያ ሶስተኛ ወንድ ልጅ (ዘፍጥ. ፳፱፥፴፬፤ ፴፭፥፳፫)። ሌዊ ከእስራኤል ጎሳዎች አንዱ አባት ሆነ።
የሌዊ ጎሳ
ያዕቆብ ሌዊንና ትውልዶቹን ባረከ (ዘፍጥ. ፵፱፥፭–፯፣ ፳፰)። የሌዊ ትውልዶች በእስራኤል ቅድስተ ቅዱሳን ቦታዎች አገለገሉ (ዘኁል. ፩፥፵፯–፶፬)። አሮን ሌዊ ነበር፣ እናም የእርሱ ትውልዶች ካህናት ነበሩ (ዘፀአ. ፮፥፲፮–፳፤ ፳፰፥፩–፬፤ ፳፱)። ሌዋውያን የአሮን ወንድ ልጆች የሆኑ ካህናትን ይረዱ ነበር (ዘኁል. ፫፥፭–፲፤ ፩ ነገሥ. ፰፥፬)። አንዳንዴም እንደ ዘማሪዎች (፩ ዜና ፲፭፥፲፮፤ ነሀ. ፲፩፥፳፪)፤ ለመስዋዕት የመጡትን የሚያርዱ (፪ ዜና ፳፱፥፴፬፤ ዕዝ. ፮፥፳)፤ እና በአጠቃላይም በቤተመቅደስ ውስጥ የሚረዱ (ነሀ. ፲፩፥፲፮) ነበሩ። ሌዋውያን ስርዓቶችን ለእስራኤል ልጆች በማከናወን ጌታን ለማገልገል የተቀደሱ ነበሩ። ሌዋውያን እራሳቸውም ለእስራኤል ልጆች ጥቅም በመስዋዕት የቀረቡም ነበሩ (ዘኁል. ፰፥፲፩–፳፪)፤ በዚህም በበኩራት ምትክ ለእርሱ የተሰጡ የእግዚአብሔር ልዩ ንብረቶች ሆኑ (ዘኁል. ፰፥፲፮)። የተቀደሱ አልነበሩም፣ ነገር ግን ለሀላፊነታቸው የጸዱ ነበሩ (ዘኁል. ፰፥፯–፲፮)። በከነዓን ውርስ ነበራቸው (ዘኁል. ፲፰፥፳፫–፳፬) አስራትን (ዘኁል. ፲፰፥፳፩)፣ አርባ ስምንት ከተማዎችን (ዘኁል. ፴፭፥፮)፣ እና በበአል ጊዜ የህዝቦችን ምፅዋት ለመቀበል መብትን (ዘዳግ. ፲፪፥፲፰–፲፱፤ ፲፬፥፳፯–፳፱) ተቀበሉ።