አህዛቦች
በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ እንደሚጠቀሙበት፣ አህዛብ የተለያዩ ትርጉሞች አሉት። አንዳንድ ጊዜ ይህም የእስራኤል ዘር ያልሆኑ ህዝቦችን፣ አንዳንድ ጊዜ የአይሁዳ ዘር ያልሆኑ ህዝቦችን፣ እናም ምንም እንኳን በመካከላቸው የእስራኤል ደም ቢኖርም፣ አንዳንድ ጊዜ ወንጌሉ የሌላቸው ሀገሮችንም ይጠቁማል። የኋለኛው የቃል ጥቅም በመፅሐፈ ሞርሞንና በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የሚጠቀሙበት ትርጉም ነው።