ሐሰት ደግሞም ሽንገላ (ውሸት)፣ መዋሸት፣ ማታለል; ታማኝ፣ ታማኝነት; ክፉ መናገር ተመልከቱ ለማታለል የሚደረግ ምንም አይነት የውሸት ንግግር። አትስረቁ፥ አትካዱም፥ ከእናንተም እርስ በርሳችሁ ሐሰት አትነጋገሩ, ዘሌዋ. ፲፱፥፲፩. ዓመፃን ጠላሁ ተጸየፍሁም, መዝ. ፻፲፱፥፻፷፫. ውሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አሰጸያፊ ነው, ምሳ. ፲፪፥፳፪. ሕዝቤ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች ናቸው, ኢሳ. ፷፫፥፰. ዲያብሎስ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነው, ዮሐ. ፰፥፵፬ (፪ ኔፊ ፪፥፲፰; ኤተር ፰፥፳፭; ሙሴ ፬፥፬). እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም, የሐዋ. ፭፥፬ (አልማ ፲፪፥፫). ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው, ፩ ዮሐ. ፬፥፳. ሐሰተኛዎች ሁሉ በሁለተኛው ሞት ክፍል አላቸው, ራዕ. ፳፩፥፰ (ት. እና ቃ. ፷፫፥፲፯). ለውሸታም ወዮለት፣ ወደታች ወደ ሲዖል ይጣላልና, ፪ ኔፊ ፱፥፴፬. ትንሽም ዋሹ በዚህ ምንም ጉዳት የለም በማለት ብዙዎች ያስተምራሉ, ፪ ኔፊ ፳፰፥፰–፱ (ት. እና ቃ. ፲፥፳፭). ለጌታ መዋሸት እንችላለን ብላችሁ ትገምታላችሁ, አልማ ፭፥፲፯. አንተ የእውነት አምላክ ነህና፣ ለመዋሸት አትችልም, ኤተር ፫፥፲፪ (ዘኁል. ፳፫፥፲፱; ፩ ሳሙ. ፲፭፥፳፱; ቲቶ ፩፥፪; ዕብ. ፮፥፲፰; ኢኖስ ፩፥፮). ሃሰት የሚናገር እናም ንሰሃ የማይገባ ወደ ውጭ ይጣላል, ት. እና ቃ. ፵፪፥፳፩. ውሸታሞቹ የቲለስቲያል ክብርን ይወርሳሉ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፹፩፣ ፻፫–፻፮. በታማኝነት እናምናለን, እ.አ. ፩፥፲፫.