የጥናት እርዳታዎች
መስዋዕት


መስዋዕት

በጥንት ቀናት፣ መስዋዕት ማለት አንድ ነገርን ወይም አንድ ሰውን ቅዱስ ማድረግ ማለት ነው። አሁን ይህም የአለም ነገሮችን ለጌታ እና ለመንግስቱ መተው ወይም መሰቃየት ማለት ነው። የጌታ ቤተክርስቲያን አባላት ሁሉንም ነገሮች ለጌታ መስዋዕት ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን ይገባቸዋል። ጆሴፍ ስሚዝ እንዳስተማረው፣ “የሁሉንም ነገሮች መስዋዕት የማይጠይቅ ሀይማኖት ወደ ህይወት እና ደህንነት የሚመራ እምነትን ለመስራት ብቁ ሀይል አይኖረውም።” በዘለአለማዊ አስተያየት፣ በመስዋዕት የሚገኙት በረከቶች ከሚተወው ነገር ሁሉ በላይ ታላቅ ናቸው።

አዳም እና ሔዋን ከዔድን ገነት ተጥለው ከወጡ በኋላ፣ ጌታ የመስዋዕት ጅግን ሰጣቸው። ይህም ህግ የመንጋቸውን በኩራት በመስዋዕይ ማቅረብን በተጨማሪ ይጠብቃል። ይህም መስዋዕት በእግዚአብሔር አንድያ ልጅ የሚደረገው መስዋዕት ምሳሌ ነው (ሙሴ ፭፥፬–፰)። ይህ ልምድ እስከ ኢየሱስ ሞት ድረስ ቀጠለ፣ የእርሱ ሞትም የእንስሣት መስዋዕትን እንደ ወንጌል ስነስርዓት አቆመው (አልማ ፴፬፥፲፫–፲፬)። ዛሬ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አባላት የቅዱስ ቁርባንን ዳቦ እና ውሀ የኢየሱስ ክርስቶስን መስዋዕት በማስታወስ ይቀበላሉ። አሁን የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት እንደ መስዋዕት የተሰበረ ልብን እና የተዋረደ መንፈስን ደግመው እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል (፫ ኔፊ ፱፥፲፱–፳፪)። ይህም እነርሱ ትሁት፣ ንስሀ የገቡ፣ እና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለማክበር ፈቃደኞች ናቸው ማለት ነው።